በልቤ ምድረ አካባጅ በሙላ ልል እልና …ቆይ እሲቲ የሚፈጠረው አይታወቅም ብዬ ማንበቤን ቀጠልኩ፡፡
ወደ መጽሃፉ ጠልቄ ስገባ አይኔን እንኳን ላለመክደን እና በፍጥነት የታሪኩ ፍፃሜ ላይ ለመድረስ ልቤ ይመታ ሰውነቴ ይግል ጀመረ …ወይ መጽሐፍ እያልኩ ወደመጨረሻው ስደርስ …
የልቤ ፍጥነት ከምንግዜውም በላይ ጨመረ በጣም ተመሰጥኩ ..እንደዚህ አይነት ፅሁፍ በማንበቤ በጣም ተደሰትኩ እንደዚህ የሚፅፍ ሰው አይጥፋ፡፡
አውነቴን ነው አንብቡት በጣም ቆንጆ መጽሐፍ ነው:: ማንበብ ግዴታ ነው ‹ መጽሐፉን › እመጓ ን
እናመሰግናለን ዶክተር አለማየሁ
ማስታወሻ
- መጽሐፉ የተመሰረተው እውነተኛ ታሪክ ላይ ነው ብዬ አምናለሁ …. ብዙ ሰው እውነት ነው አይደለም እያለ ሲከራከር ሰምቻለሁ ….እኔ ግን እውነተኛ ታሪክ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡
- ዲያቆን ብርሃኑ አድማሴ በ እመጓ መጽሐፍ በስተጀርባ ሽፋን ላይ ስለ መጽሐፉ አስተያየቱን ሲሰጥ … እራሳችሁ አንብቡት፡፡
- ከመጽሐፉ ውስጥ ትንሽ ነገር ቆንጥሬ በሌላ ጊዜ ይዤ እመለሳለሁ፡፡